ንግድ ባንክ
10005357725661
loading
0%
ስር ነቀልና ስርአቱን የጠበቀ እንዲሁም ተደራሽነት ባለው መልኩ መሰረታዊ የዲን እውቀትን ማስፋፋት፣
ከፍተኛ ንቅናቄ የሚፈጥሩ የዳዕዋ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፣
በየ አካባቢው ከአካባቢው ልጆች ጋር በመተባበር የዳዕዋ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፣ደረጃውን የጠበቀ የቁርዓን ሂፍዝና አጠቃላይ የዲን ትምህርት መማሪያ ተቋም (መርከዝ) መክፈት፣
ኡስታዞች በታላላቅ መሻይኾች ( ኡስታዞች) የትምህርት አሰጣጥ ሂደትና ሌሎችንም ተያያዥ ነገሮች በተመለከተ አጫጭር ኮርሶችን ማዘጋጀትና እንዲሁም መስጂዶቻቸው የመድረሳ ሂደት እንዲኖራቸው ማስቻል፣
ለአካዳሚክ ተማሪዎች የተለያዩ ኮርሶችን ማዘጋጀት፣ከ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ተማሪዎች ጀማዓ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መፍጠርና ስራዎችን በጋራ መስራት:በተለያዩ ርእሶች ጊዜውን ጠብቆ የሚታተሙ ፓንፕሌቶችን ማዘጋጀት፣
መንፈሳዊ ህክምና ( የሩቃ) ማእከል ማደራጀት፣መገንባትና አስፈለጊ የሆኑ ግብአትችን ማቅረብ እንዲሁም የቅርብ ክትትል ማድረግ፣
የልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት መክፈት
ወላጅ አልባ ሕፃናት(የቲሞችን ) መርዳትና መንከባከብ
አቅመ ደካሞችን፣ የተቸገሩና ረጂ የሌላቸውን እንዲሁም ባላቸው የሞተባቸውን( ጋለሞታዎችን) መርዳትና መንከባከብ
ይህንን ስራ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ላይ በስፋት መስራት፣
ከመሰል እስላማዊ ማህበራት ጋር በጋራ መስራትና ድጋፍ መሰጣጠት
ማህበረሰባችን ከሙስሊም አመራሮችና ከአገልግሎት ሰጪ አካላት(ሲቪል ሰርቫንቱ) ጎን እንዲቆምና በመሀከላቸው ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ማስቻል
ማህበረተሰባችን ተጠቃሚ የሚያደረጉ እና ለወጣቱ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ የተለየዩ የልማት ሥራዎች መሰራት
ማህበረሰባችን የሚያስተሳስሩ እንደ ት/ት፤ የተለያዩ የልማት እና የቢዝነስ ስራዎችን ( አክሲዮን ….) ማደራጀት፣
ማህበረተሰባችን ውስጥ ያለዉ ዕውቀት ፣ ብር፣ ጊዜ እና ጉልበት በስርዓቱ አቀናጅቶ መጠቀም
ማህበረተሰብ እርስ በርሱ የሚያስተሳሰሩ ሥራዎች መሰራት፣
ማህበረሳችን ለአካዳሚክ ትምህርት ያለውን አመለካከት ማሳደግና አስፈላጊነቱን ማስገንዘብ፣
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከተዋቀሩ የሂዳያ ጀማዓዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ስራዎችን መስራት
ገጠርና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ከሚገኙ ጀመዓዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ስራዎችን መስራት
እስከታችኛው መንደር ቀበሌ ድረስ መዋቅሮችን መዘርጋትና ስራዎችን መስራት፣
በተመረጡ መስጂዶች ኢንፎርሜሽን ኮሚኔኬሽን ሴንተሮችና ላይብረሪዎች ማቋቋም እና ስልጠና መስጠት
ተማሪዎች በትምህርት እና በዲናቸው ውጤታማ የሚሆንባቸው መንገድ በስልጠና ግንዛቤ ማስጨበጥ
የህክምና የሚያስፈልጋቸው አቅመ ደካሞች ተገቢ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣
ለየቲሞች፣ለአቅመ-ደካሞች፣እና ለአዳዲስ ሰለምቴዎች የኢስላማዊና አካዳሚክ ትምህርት እድል መፍጠር እና በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ማድረግ፡፡
የዳዕዋ ፕሮግራሞችን፣ወርክሾፖችን፣ሲምፖዝየሞችንና ሴሚናሮችን ማዘጋጀት፣
ለድርጅቱ የገቢ ምንጭ የሚሆኑ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎችን መስራት
ኢስላማዊ ካሪኩለምን ያካተቱ አካዳሚክ ት/ቤቶችን መገንባት፣
በኢስላማዊ ማንነት ስነምግባር የታነፀ ወጣት ከመፍጠር አንጻር በልዩ ትኩረት መስራት፡
ሙስሊሞች እምነታቸውን ቀደምት ሙስሊሞች (ሰሐቦች) እምነታቸውን በመሰረቱበት ቁርዓንና ሐዲስ ላይ እንዲገነቡ ማገዝ፡፡